ቋሚ የድርጅት ጠበቃ
ድርጅታችን ኤ እና ኤም ኢንጅነሪንግ የሚመለከቱ የሕግ ጉዳዮችን በመከታተል፣ ውሎችን በማዘጋጀትና በመመርመር፣ እንዲሁም የሕግ ምክርና ድጋፍ በመስጠት የሕግ ክፍል ስራዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲከናወኑ መደገፍ። የውል ዝግጅትና ምርመራ: የተለያዩ የንግድ፣ የስራ እና የአገልግሎት ውሎችን ማዘጋጀት፣ መመርመርና ማሻሻል፤ የሕግ ምርምር (Legal Research): ከተቋሙ አሰራር ጋር የሚሄዱ አዳዲስ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን መመርመርና ት
ድርጅታችን ኤ እና ኤም ኢንጅነሪንግ የሚመለከቱ የሕግ ጉዳዮችን በመከታተል፣ ውሎችን በማዘጋጀትና በመመርመር፣ እንዲሁም የሕግ ምክርና ድጋፍ በመስጠት የሕግ ክፍል ስራዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲከናወኑ መደገፍ።
- የውል ዝግጅትና ምርመራ: የተለያዩ የንግድ፣ የስራ እና የአገልግሎት ውሎችን ማዘጋጀት፣ መመርመርና ማሻሻል፤
- የሕግ ምርምር (Legal Research): ከተቋሙ አሰራር ጋር የሚሄዱ አዳዲስ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን መመርመርና ትንተና ማቅረብ፤
- የክስና ክርክር ዝግጅት: ከፍርድ ቤት፣ ከስራ ክርክርና ከስምምነት ውጪ ከሆኑ ውዝግቦች ጋር የተያያዙ ማመልከቻዎችን፣ የመከላከያ መልሶችንና ሌሎች የሕግ ሰነዶችን ማዘጋጀት፤
- አስተዳደራዊ እና ስነ-ሰነድ ስራዎች: የሕግ መዝገቦችን፣ ውሎችንና የፍርድ ቤት ፋይሎችን በአግባቡ ማደራጀትና መጠበቅ፤
- የሕግ አማካሪነት ድጋፍ: ለተለያዩ የድርጅቱ ክፍሎች የመጀመሪያ ደረጃ የሕግ ማብራሪያና ድጋፍ መስጠት።
A and M Engineering PLC
የቢሮው ትክክለኛ ቦታ ገና አልተረጋገጠም — ከመሄድዎ በፊት በስልክ ያረጋግጡ።
ምንጭ · Source: Ethiojobs · ማመልከትዎ በፊት ከቀጣሪው ያረጋግጡ።