BinaSmart ሥራ 💼 Own a company?
አማርኛ A and M Engineering PLC

የግል ረዳት (Personal Assistant)

የግል ረዳት የስራ መግለጫ የስራ አስፈፃሚውን ዕለታዊ የቀን መቁጠሪያ፣ ቀጠሮዎች፣ ስብሰባዎች እና መርሃ ግብሮች ማስተባበር እና መፈፀም። የጉዞ ዝግጅቶችን ማስተባበር፤ በረራዎችን፣ ሆቴሎችን፣ መጓጓዣዎችን እና የጉዞ መርሃ ግብሮችን መከታተል እና ማቀናጀት። ኢሜሎችን፣ የስልክ ጥሪዎችን እና ሌሎች ደብዳቤዎችን ተገቢውን ምላሽ መስጠትና መከታተል። ሰነዶችን፣ ሪፖርቶችን፣ አቀራረቦችን፣ ፕረዘንቴሽን እና የስብሰባ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት። ስብሰባዎችን

📍 hayle garment💼 Full time 🗓 17 Oct 2026 · 26 days left

የግል ረዳት የስራ መግለጫ

  • የስራ አስፈፃሚውን ዕለታዊ የቀን መቁጠሪያ፣ ቀጠሮዎች፣ ስብሰባዎች እና መርሃ ግብሮች ማስተባበር እና መፈፀም።
  • የጉዞ ዝግጅቶችን ማስተባበር፤ በረራዎችን፣ ሆቴሎችን፣ መጓጓዣዎችን እና የጉዞ መርሃ ግብሮችን መከታተል እና ማቀናጀት።
  • ኢሜሎችን፣ የስልክ ጥሪዎችን እና ሌሎች ደብዳቤዎችን ተገቢውን ምላሽ መስጠትና መከታተል።
  • ሰነዶችን፣ ሪፖርቶችን፣ አቀራረቦችን፣ ፕረዘንቴሽን እና የስብሰባ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት።
  • ስብሰባዎችን ቀጠሮዎችን፣ ኢግዚቪሽኖችን ማቀናጀትና ማስተባበር፤
  • የስብሰባ ቃለ-ጉባኤ ማስታወሻዎችን መያዝ፣ መዝገቦችን መጠበቅ እና የድርጊት ነጥቦች ከተሰጡ በኋላ የታዘዙ የሥራ አፈፃፀም መከታተል።
  • ሚስጥራዊ እና አስፈላጊ መረጃዎችን በጥንቃቄ መያዝ ምስጢራዊነትን በመጠበቅ።
  • ኤሌክትሮኒክስ እና አካላዊ ፋይሎችንና ሰነዶችን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ማደራጀት እና መያዝ።
  • የድርጅቱን እና ለግል ፍላጎቶች ጥናቶችን ማድረግ እና መረጃዎችን መሰብሰብ።
  • የወጪ እና የገቢ አካሄድ እና ደረሰኝ ተከታትሎ ከሂሳብ ክፍል ጋር ማስታረቅ።
  • በስራ አስፈፃሚው፣ በሰራተኞች፣ በደንበኞች፣ በአቅራቢዎች እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ሥራ ግንኙነት ማስተባበር።
  • የግል እና የሥራ ነክ ጉዳዩች ከሚመለከተው አካል ጋር ጉዳዩን ለማየት ቀጠሮ ማስያዝ።
  • መልዕክቶችን ማድረስ እና እንዳስፈላጊነቱ የግል ጉዳዮች ላይ ዕርዳታ መስጠት።
  • የቀጠሮዎችን የመጨረሻ ቀናቶችን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዩች ማስታወስ።
  • እንደአስፈላጊነቱ ፕሮጀክቶችን እና አስተዳደራዊ ስራዎችን መደገፍ።
  • የተደራጀ እና ምቹ የሆነ የስራ አካባቢን መፍጠር።
  • የስራ አስፈፃሚውን ፍላጎቶች አስቀድሞ መገመት እና የስራ መርሃ ግብር ወይም አስተዳደራዊ ችግሮችን በንቃት መፍታት።
  • ማይክሮሶፍት ኦፊስ፣ ጎግል ብቃት ያላት፣ የቀን መቁጠሪያ መተግበሪያዎችን እና ሌሎች መገልገያዎች መጠቀም።
  • በማንኛውም ጊዜ ሙያዊ ብቃትን፣ አስተማማኝነትን፣ ምስጢራዊነትን እና እጅግ በጣም ጥሩ ግንኙነትን መጠበቅ።
  • በ ISO እና ERP ሲስተሞች ላይ ቀልጣፋ መሆን።
  • ስራ አስፈፃሚዎችን በማንኛውም ጊዜ መደገፍ።

ቁልፍ ክህሎቶች

  • እጅግ በጣም ጥሩ ድርጅታዊ እና የጊዜ አያያዝ ክህሎት።
  • ጠንካራ የጽሁፍ እና የቃል ክህሎት በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ።
  • ለዝርዝር ነገሮች ትኩረት መስጠት።
  • ምስጢራዊነትን መጠበቅ።
  • ብዙ ስራዎችን በአንድ ጊዜ ማከናወን እና ቅድሚያ መሰጠት የሚገኝባቸውን መስጠት።
  • ችግር የመፍታት ክህሎቶች።
  • ሙያዊ የሰዎች ግንኙነት ክህሎት።
  • የቀን መቁጠሪያ እና የጉዞ አስተዳደር።
  • ማይክሮሶፍት ኦፊስ ጎግል እውቀት።
  • ራስን ችሎ የመስራት ችሎታ።
  • ተለዋዋጭነት እና ከሁኔታዎች ጋር መላመድ።
  • ጠንካራ ክትትል እና የስራ አስተዳደር ክህሎቶች።

 

 

📨 Apply here

Send your CV here — we pass it to this employer.

A and M Engineering PLC A and M Engineering PLC
The exact office location is not confirmed yet — call before travelling.
See every vacancy from this employer →

ምንጭ · Source: Ethiojobs · Confirm with the employer before applying.

More from A and M Engineering PLC

አይሲቲ ኦፊሰር

📍 Addis Ababa🗓 3 Oct 2026 · 12 days left

Senior Accountant

📍 Addis Ababa🗓 16 Oct 2026 · 25 days left

Executive secretary

📍 Haile Garment🗓 16 Oct 2026 · 25 days left

የጥራት ቁጥጥር (Quality Control)

📍 Addis Ababa🗓 16 Oct 2026 · 25 days left

ንብረት ተቆጣጣሪ (Storekeeper)

📍 Addis Ababa🗓 8 Oct 2026 · 17 days left